ሜሪካዊው የአጭር ርቀት ኮከብ ኖዋህ ላይልስ በሽርፍራፊ ስከንዶች ልዩነት የ100 ሜትር ኦሊምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆነ።
ላይልስ በአስደናቂ ሁኔታ አሸናፊው በፎቶ በተለየበት ውድድር ጃማይካዊውን ኪሻኔ ቶምፕሰን በመርታት ነው የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነው።
ሁለቱም አትሌቶች የ100 ሜትሩን ውድድር በ9.79 ሰከንድ ቢያጠናቅቁም ላይልስ በአምስት አንድ ሺህኛ ሰከንድ ቀድሞ በመግባት ድል ተቀዳጅቷል።
በኦሊምፒክ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተሳተፈ የሚገኘው ቶምፕሰን ውድድሩን እየመራ ቢዘልቅም በመጨረሻዎቹ ሰከንዶች በላይልስ ተበልጧል።
በፓሪስ ኦሊምፒክ በአራት የተለያዩ ውድድሮች አራት የወርቅ ሜዳሊያዎች ለማምጣት እየተፎካከረ ያለው ላይልስ የመጀመሪያውን በድል ተወጥቷል።
አሜሪካዊው የቀድሞው የዓለም ሻምፒዮና ፍሬድ ከርሊ በ9.81 ሰከንድ ሶስተኛ ሲወጣ ደቡብ አፍሪካዊው አካኒ ሲምቢኔ አራተኛ ሆኖ አጠናቋል።
ስታድ ደ ፍራንስ የነበረው ጢም ያለው ተመልካች በጉጉት ሲጠባበቀው የነበረው የ100 ሜትር ፍፃሜ ለደቂቃዎች አርፍዶ ቢጀምርም አስደናቂ ውድድር አሳይቷል።
በጣም ፉክክር በተስተዋለበት ፍልሚያ ስምንቱም ተፋላሚዎች ከላይልስ በ0.12 ሰከንድ ልዩነት ነው የገቡት።
የብሪታኒያዎቹ ዣርኔል ሂዩስ እና ሉዊ ሂንችክሊፍ ወደ ፍፃሜው ማለፍ ሲሳናቸው ያለፈው ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ማርሴል ጄኮብስ እና ጃማይካዊው ኮከብ ኦብሊክ ሴቪል ከሜዳሊያ ፉክክሩ ውጭ ሆነዋል
.